ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለይፋዊ ስራ ጉብኝት ኬንያ ሞያሌ ገብተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ሞያሌ ሲደርሱ የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
መሪዎቹ የሐዋሳ-ቡሌ ሆራ-ያቤሎ-ሜጋ-ሞያሌ መንገድና የጋራ ፍተሻ ጣቢያ ፕሮጀክትን መርቀው ከፍተዋል።
500 ኪ.ሜ ርዝመት ያለውና የሞምባሳ-ናይሮቢ-አዲስ አበባ ኮሪደር አካል የሆነው መንገዱ ኢትዮጵያን ከኬንያ የሚያስተሳስር መሆኑ ተገልጿል።
የሐዋሳ-ቡሌ ሆራ-ያቤሎ-ሜጋ-ሞያሌ የአስፓልት ኮንክሪት መንገድ 6 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ወጪ እንደተደረገበት ተገልጿል። ዘገባው የኢቢሲ ነው።#አዲስ_ነገር #Whatsnew_ebs