EthiopiaNews

ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን አካታች የምክክር ጉባኤ ለማካሄድ አሁንም ወደ ምክክሩ ለሚመጡ አካላት በሩ ክፍት መሆኑን ገለጸ

የመጨረሻው የምክክር ምእራፍ ላይ ቢሆንም አካታች የምክክር ጉባኤ ለማካሄድ በማንኛውም ጊዜ ወደ ምክክሩ ለሚመጡ አካላት በሩ አሁንም ክፍት መሆኑን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ ይሄንን ያስታወቀው በኦሮሚያ ክልል በትጥቅ ትግል ላይ ቆይተው ከተመለሱ አካላት ጋር ውይይት ባካሄደበት ወቅት ሲሆን አካታች የምክክር መድረክ ለማካሄድ እስካሁን በምክክሩ ላልተሳተፉ አካላት በሩ ክፍት መሆኑን ነው የገለጸው፡፡

የውይይት መድረኩን በንግግር የከፈቱት ዋና ኮሚሽነር መስፍን ዓርዓያ በክልሉ ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩና በአሁኑ ሰዓት ሰላምን መርጠው ለተመለሱ አካላት የሰላምን መንገድ መርጠው በመምጣታቸው ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን መድረኩ የቀሩ ወገኖችን ወደ ሰላም ለማምጣት የሚያስችል መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

ዛሬ በጀመረውና እስከ ነገ ድረስ በሚቆየው በዚህ የውይይት መድረክ ተሳታፊዎች አጀንዳቸውን ለኮሚሽኑ እንደሚያስረክቡም ይጠበቃል፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv