EthiopiaNews

የፀረ-ተህዋሲያን መድሃኒቶች በጀርሞች መለመድ በሽታ ፈዋሽነታቸውን እንዲያጡ እያደረገ ነው ፡፡

የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን የፀረ-ተህዋሲያን መድሃኒቶች በጀርሞች መለመድ የዓለም ትልቁ ስጋት መሆኑን ገልጿል፡፡

ባለስልጣኑ ይሄንን ያለው የፀረ-ተህዋሲያን መድኃኒቶች በጀርሞች መለመድ የግንዛቤ ማስጨበጫ ቀን ባከበረበት ወቅት ሲሆን ያለ አግባብ መድሃኒቶቹን መጠቀም በተዋህስያን በቀላሉ እንዲለመዱና በሽታ ፈዋሽነታቸውን እንዲያጡ እያደረገ መሆኑንም ጠቅሷል፡፡

አግባብ ያልሆነ የፀረ-ተዋህሲያን መድሃኒቶችን መጠቀም፣ ከትዕዛዝ ውጪ መድሃኒቶችን ጨምሮና ቀንሶ መውሰድ፣ የግልና የአከባቢ ንፅህናን አለመጠበቅ እና መሰል ጥንቃቄ የጎደላቸው ተግባራት ችግሩን ከሚያስከትሉ መንስኤዎች መካከል መሆናቸውንም ነው ባለስልጣኑ ያነሳው፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv