EthiopiaNews

ዳንጎቴ ኩባንያ ከአለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን የ600 ሚሊየን ዶላር ብድር አገኘ።

የአፍሪካ ፋይናንስ ኮርፖሬሽን በምህፃረ ቃሉ ኤኤፍሲ በኢትዮጵያ እና በናይጄሪያ የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ እያካሄደ ላለው የዳንጎቴ ኩባንያ የ600 ሚሊየን ዶላር ብድር መፍቀዱን አስታወቀ።

በ ኤኤፍሲ የፀደቀው ብድር ዳንጎቴ በኢትዮጵያ እየገነባ ያለውን የማዳበሪያ ፋብሪካ የሚደግፍ እና የናይጄሪያውን የማዳበሪያ ፋብሪካ አመታዊ የ3 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ምርት ወደ 9 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን እንዲያድግ የሚያግዝ ነው ተብሏል።

ዳንጎቴ በናይጄሪያ ባለው የማዳበሪያ ፋብሪካ ላይ የሚያካሂደው የማስፋፊያ መርሃ ግብር ሲጠናቀቅ ኩባንያው በሚቀጥሉት 3 አመታት ከማዳበሪያ ሽያጭ ከ4 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ እንደሚያስገባ ገልጿል። መረጃው ከአፍሪካ ፋይናንስ ኮርፖሬሽን የተገኘ ነው፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews