ለኤርትራዊያን መንገደኞች
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አስመራ የሚጓዙ ደንበኞቹን ከመጉላላት ለመታደግ አስፈላጊውን ሁሉ የበረራ አማራጭ እያቀረበ እንደሆነ ገለፀ።
መ/ቤቱ የአስመራ ደንበኞቹን በተለያዩ አየር መንገዶች ወደ መዳረሻቸው እያደረሰ መሆኑን ገልጾ ወደ አለምአቀፍ የጥሪ ማዕከላችን 6787 በመደወል እና 5 ቁጥርን በመጫን ለእናንተ ብቻ በተዘጋጀ የበረራ አማራጭ እንድትጠቀሙ ሲል ጥሪውን አቅርቧል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከትላንት ነሐሴ 28/2016 ጠዋት ጀምሮ ወደ ኤርትራ አስመራ የሚያደርገውን በረራ ማቆሙን መግለፁ ይታወቃል።