CANAL+
ታዋቂው የፈረንሣይ የክፍያ-ቴሌቪዥን ሳተላይት ኦፕሬተር በኢትዮጵያ ሲያካሂድ የነበረውን ቴሌቪዥን ስርጭት ከ4 ወራት በኋላ ሙሉ በሙሉ እንደሚያቆም አስታወቀ።
የካናል ፕላስ እና የንግድ አጋሩ ብሩህ ኢንተርቴይመንት ከአውሮፓውያኑ 2021 ጀምሮ በክፍያ አማራጭ ሲያስራጩት የነበረው የሳተላይት የቴሌቪዥን ስርጭት ከ4 ወራት በኋላ አቁም ወደ ቴሌቭዥን ፕሮግራም ይዘቶች ና ፊልም ዝግጅት ቢዝነሱን ለመቀየር መወሰኑን ለጣቢያችን ኢቢኤስ ቴሌቪዥን በላው መግለጫ ይፋ አድርገዋል።
የ ሳተላይት የቴሌቭዥን ስርጭቱን ያቆመው የካናል ፕላስ ከብሩህ ኢንተርቴይመንት ድርጅት ጋር በቢሚዲያ በተባለ ልዩ ማዕቀፉ በኩል የተለያዩ የቴሌቭዥን ፕሮግራሞችን እንዲሁም ፊልሞችን እንደሚሰራ እና አርቲስቶችን የመደገፍ ስራዉን የሚቀጥል ይሆናል ተብሏል።