EthiopiaNews

ሕገወጥ የወርቅ ንግድ

የገቢዎች ሚኒስቴር በሕገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ አምስት ኪሎግራም ጥፍጥፍ ወርቅ መያዙን አስታወቀ።

በአዲስ አበባ ኤርፖርት በቁጥጥር ስር የዋለው የወርቅ ጥፍጥፍ፣ ከዱባይ ወደ ኢትዮጵያ የተጓዘች መንገደኛ ሴት በለበሰችው ጃኬት በመደበቅ እና በወገቧ በመጠምጠም ለማሳለፍ ስትሞክር በአካላዊ ፍተሻ የተያዘ ነው።

ተጠርጣሪዋን በሕግ ጥላ ስር በማዋል የአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ባለሙያዎች ተጠርጣሪዋ ላይ ተጨማሪ ምርመራ እያደረጉባት ይገኛል።

መረጃው ከገቢዎች ሚኒስቴር የተገኘ ነው።

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv