በኤምሬትስ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን
ከ300 ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን በዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ ውስጥ እንደሚኖሩ በዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ጀማል በክር ገለፁ፡፡
አምባሳደሩ ከኤምሬትስ ኒውስ ኤጀንሲ ጋር በነበራቸው ቃለ ምልልስ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት በጋራ መተማመን፣ ሰላምና እድገትን መሰረት ያደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ከ130 በላይ የኤመሬትስ ኩባንያዎች ከ160 በላይ በሚሆኑ ፕሮጀክቶች ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን የጠቀሱት አምባሳደሩ በኢትዮጵያ ውስጥ በግብርና፣ ማኑፋክቸሪንግ፣ ማእድንና ቱሪዝም ዘርፎች የኢንቨስትመንት እድሎች መኖራቸውን መናገራቸውንም ጠቅሰዋል፡፡
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
