ማረሚያ ቤቶቻችን ሲፈተሹ
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በሚገኙ 26 ማረሚያ ቤቶች ባደረኩት ምልከታ ታራሚዎች ያለ ክስ እና ያለ ፍርድ ለረጅም ጊዜ ታስረው እንደሚገኙ አረጋግጫለሁ ብሏል።
የኢሰመጉ 155ኛ ልዩ መግለጫ በሚል ጉባኤው ባወጣው ሪፖርት እንዳለው ማረሚያ ቤቶቹ መያዝ ከሚችሉት ታራሚዎች በላይ በመያዝ ተጨናንቀው እንደሚገኙ እና በቂ አየር የማያስገቡ መሆናቸውን ጭምር ታዝቤያለሁ ብሏል።
በተጨማሪም አብዛኛዎቹ ማረሚያ ቤቶች የማረምና የማነጽ ተግባራቸውን በአግባቡ እንደማይወጡ እና የአመክሮና ይቅርታ አሰጣጡም ግልጽነት የጎደለው ነው ያለ ሲሆን የይቅርታ አሰጣጥ መመሪያውም ለአፈጻጸም ምቹ አለመሆኑን ለማወቅ ችያለሁ ሲል ገልጿል።