ማስጠንቀቂያ ለስደተኞች
በቀጣይ ቀናት ውስጥ በደቡብ አፍሪካ የሚካሄዱ ፀረ ስደተኞች ተቃውሞ ሰልፎችን ተከትሎ በስደተኞችና ንብረታቸው ላይ ጥቃት ሊፈጸም ስለሚችል በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ስደተኞች ከፍተኛ ጥንቃቄ አንዲያደርጉ ማስጠንቀቂያ ተላለፈ።
በርካታ የአፍሪካ ሀገራት በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ዜጎቻቸው በቀጣይ ቀናት ውስጥ ደህንነታቸውን ለመጠበቅ አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስዱ በማሳሰብ ላይ ይገኛሉ፡፡
ለአብነት የጋና መንግስት ፀረ ስደተኞች ተቃውሞ በሚካሄድባቸው ቀጣይ ቀናት ውስጥ ዜጎቹ የንግድ ተቋማቶቻቸውን እንዲዘጉና ከቤት እንዳይወጡ ጥሪ ሲያቀርብ በደቡብ አፍሪካ የናይጄሪያ ህብረት ደግሞ በተመሳሳይ ናይጄሪያዊያን ከቤታቸው እንዳይወጡ አስጠንቅቋል፡፡
በደቡብ አፍሪካ መዲና ፕሪቶሪያ በቀጣይ ረቡዕ ግዙፍ ፀረ ስደተኞች ተቃውሞ ሰልፍ ይካሄዳል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ከዚያ ቀጠሎ በጁሀንሰበርግ መሰል ፀረ ስደተኞች ተቃውሞ ሰልፎች ይካሄዳሉ መባሉ ተነግሯል፡፡
በደቡብ አፍሪካ ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ 2 ነጥብ 4 ሚሊዮን የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ስደተኞች የሚኖሩ ሲሆን እነዚህ ስደተኞች ከደቡብ አፍሪካ አጠቃላይ ሕዝብ ውስጥም 4 በመቶውን እንደሚሸፍኑ ጠቅሶ የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
