EthiopiaNews

የሚኒስቴሩ ማሳሰቢያ

በነዳጅ እጥረት ምክንያት የተፈጠሩ የትራንስፖርት አገልግሎት መስተጓጎሎች ሙሉ በሙሉ እንዲቀረፉና ከአዲስ አበባ እስከ ክልሎች ድረስ ታሪፍ በተወሰነዉ መሰረት ብቻ እንዲቀጥል ጥብቅ ክትትል እንደሚደረግ የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር አሳሰበ፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባወጣው መግለጫ የነዳጅ አቅርቦት ወደ መደበኛ ሁኔታው መመለሱ በትራንስፖርት ዘርፍ የተፈጠሩ መስተጓጎሎች በፍጥነት እንዲፈቱ ያስችላል ነው ያለው።

አክሎም የህዝብ ኑሮ መረጋጋትን ለማረጋገጥና የትራንስፖርት አገልግሎት በዘላቂ መልኩ እንዲጠናከር እንደሚሰራም ጠቅሷል፡፡

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews