EthiopiaNews

የመንግስት የበጀት ጉድለት

መንግስት በተያዘው የ2018 ግማሽ አመት የ93 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር የበጀት ጉድለት እንደገጠመው የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ ይሄንን ያስታወቀው የ2018 ግማሽ አመት አፈፃፀም በተመለከተ ዛሬ ባወጣው ሪፖርት ላይ ነው።

የፌዴራል መንግስት በግማሽ አመቱ 704 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ማስገባቱን እንዲሁም 798 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ወጪ ማድረጉን የገለጸው ሚኒስቴሩ የ93 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ጉድለት ማጋጠሙንና ይሄንን ክፍተት ለመሙላት ከሃገር እና ከውጪ ምንጮች እንደሚሸፍን ገልጿል።

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews