በቁጥጥር ስር የዋሉ ስደተኞች
ኡጋንዳ ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ 231 ስደተኞችን በቁጥጥር ስር ማዋሏን አስታወቀች፡፡
የኡጋንዳ የአገር ውስጥ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ በቁጥጥር ስር የዋሉት ስደተኞች የኢትዮጵያ፣ ናይጄሪያ፣ ፓኪስታን፣ ህንድ፣ ባንግላዲሽ፣ ጋና፣ ማይናማር፣ ሲሪላንካ፣ ካምቦዲያና ማሌዥያ ዜግነት ያላቸውን መሆናቸውን ገልጿል፡፡
ከእነዚህ በቁጥጥር ስር ከዋሉት ስደተኞች መካከልም 169 የሚሆኑት በካምፓላ ውስጥ በሚገኘው ቡኮቶ በተሰኘው ሰፈር አንድ ሙሉ ህንፃን ተከራይተው የተገኙ መሆናቸውን እንዲሁም የተያዙት 231 ስደተኞች ወደ ኡጋንዳ የተጓዙት በሌላ አገር ስራ እንደሚያገኙ ቃል ተገብቶላቸው መሆኑን ነው የተገለጸው፡፡
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
