ምርጫ ቦርድ ለምርጫው የድምጽ መስጫ ቁሳቁሶችን ከትናንት ምሽት ጀምሮ ማጓጓዝ መጀመሩን አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 14/2013 ዓ.ም ለሚከናወነው የመጀመሪያው ዙር ምርጫ የድምጽ መስጫ ቁሳቁሶችን ከትናንት ምሽት ጀምሮ ማጓጓዝ መጀመሩን አስታውቋል።ቦርዱ ከምርጫ ቁሳቁስ ስርጭት በተጨማሪ የምርጫ አስፈጻሚዎች ስልጠና በ460 የምርጫ ክልሎች ከቅዳሜ ማለትም ከሰኔ 10/2013 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ፣ ድሬዳዋና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ላይ እየሰጠ እንደሚገኝ ጠቅሶ በቀጣዮቹ ቀናት በተቀሩት ቦታዎች ስልጠናው እንደሚቀጥል ገልጿል።በቦርዱ እውቅና ከተሰጣቸው 167 የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች መካከል 102ቱ ህብረተሰቡ ድምጽ እንዲሰጥ የማስተማርና ለመራጮች መረጃ የመስጠት ስራቸውን እየሰሩ እንደሚገኙም ተነግሯል። እስካሁን ወደ 45 ሺህ ለሚጠጉ የአገር ውስጥ የምርጫ ታዛቢዎች ባጅ መስጠቱንና ቁጥሩ ሊጨምር እንደሚችል የገለጸው ቦርዱ የውጭ አገራት ታዛቢዎችን በተመለከተ ደግሞ ለምርጫው ጥቂት ቀናት እስኪቀሩት ድረስ የሚመጡ በመሆኑ አጠቃላይ የምርጫ ታዛቢዎች ቁጥሩ ሊጨምር እንደሚችል ነው ቦርዱ ያመለከተው።የደቡብ ምዕራብ ክልል ህዝበ ውሳኔን በተመለከተ ደግሞ ቦርዱ ከአካባቢው አመራሮችና ተወካዮች ጋር ከተነጋገረ በኋላ የደረሠበት ውሳኔ አለመኖሩን በመጥቀስ በቀጣዮቹ 2 ቀናት ውስጥ ግን ውሳኔውን ለመገናኛ ብዙሃን እንደሚገልጽ በትላንቱ መግለጫው ጠቁሟል።

#አዲስነገር#WhatsNew