LatestNews

ምርጫ ቦርድ ያዘጋጀውን የአሰራር መመሪያ ለፖለቲካ ፓርቲዎችና ለመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ይፋ አድርጓል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከምርጫ ዋዜማ እስከ ድህረ ምርጫ ድረስ የሚኖረውን ሂደት ፍትሃዊና ተዓማኒ ለማድረግ በሚል ያዘጋጀውን የአሰራር መመሪያ ለፖለቲካ ፓርቲዎችና ለመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ይፋ አድርጓል። ቦርዱ የምርጫ ቁሳቁስ አከፋፈልና አረካከብን፣ በምርጫ እለት በየምርጫ ጣቢያው የሚገኙ አስፈጻሚዎች ስለሚያደርጓቸው እያንዳንዱ የስራ እንቅስቃሴዎች እንዲሁም የድምጽ አሰጣጥና የድምጽ ቆጠራ ሂደትን ጨምሮ መሰል በምርጫ እለት የሚከናወኑ ተግባራት ምን እንደሚመስሉ አመላክቷል። ከዚህ በተጨማሪም ከኮሮጆ አስተሻሸግ ደህንነትና ሚስጥራዊነት ባሻገር በትክክል ድምጽ የተሰጠባቸውን፣ የተበላሹትን እንዲሁም ምንም አይነት ምልክት ያልተደረገባቸው የድምጽ መስጫ ወቀረቶች የመለየት ሂደትን ያካተተ ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡ቦርዱ አክሎም በምርጫው የሚሳተፉ የምርጫ ታዛቢዎች፣ የምርጫ ጣቢያ ሰራተኞች፣ የጸጥታና ደህንነት አካላት እንዲሁም ሌሎች የሚመለከታቸው ሁሉ ቦርዱ ያስቀመጠውን ሂደት መከተል እንደሚገባቸው ገልጿል።