LatestNews

የቡድን ሰባት ሀገራት በትግራይ የሰብዓዊ እርዳታ እንዲቀርብ ሁኔታዎች ሊመቻቹ ይገባል እያሉ ነው፡፡

ከሰሞኑ በብሪታኒያ ስብሰባ የተቀመጡት #የቡድን_ሰባት ሀገራት በትግራይ የሰብዓዊ እርዳታ እንዲቀርብ ሁኔታዎች ሊመቻቹ ይገባል እያሉ ነው፡፡የቡድን ሰባት ሀገራት እንደሚሉት የመንግሥታቱ ድርጅት ለረሀብ ተጋለጠዋል ያላቸው 350 ሺህ ሰዎች እርዳታ እንዲቀርብላቸው ሁኔታዎች ሊመቻቹ ይገባል ያሉ ሲሆን በትግራይ የተኩስ አቁም እንዲደረግና የኤርትራ ወታደሮች ከክልሉ እንዲወጡም ጠይቀዋል፡፡የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ በትግራይ ረሀብ አለ የሚለውን ክስ በተደጋጋሚ ውድቅ ያደረገ ሲሆን የኤርትራ ወታደሮችም ከትግራይ እየወጡ መሆኑን ይገልፃል፡፡ በተመሳሳይ የአውሮፓ ህብረት መቀመጫ ብራስልስን የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን መጎብኘታቸውን ተከትሎ አሜሪካና ህብረቱ ትግራይን አስመልክቶ ተመሳሳይ የጋራ መግለጫ አውጥተዋል፡፡አሜሪካና የአውሮፓ ህብረት እንደሚሉት በትግራይ ግጭቱ ከተቀሰቀሰ ጀምሮ ሁኔታዎች እየከፉ መጥተዋል፡፡ ይኸው መግለጫም በትግራይ 400 ሺህ ሕዝብ ለረሀብ ተጋልጧል ይላል፡፡ የምዕራባዊያን ክስን በተመለከተ ተደጋጋሚ ማስተባበያ የሚሰጠው የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ ክልል አለ የሚባለው የረሃብ ስጋት ሀሰት መሆኑን በመግለጽ ምዕራባዊያን በተመሳሳይ ክስ ከመጠመድ ይልቅ በቂ እርዳታ ለተራድኦ ድርጅቶች ቢለግሱ ተገቢ ነበር ይላል፡፡