LatestNews

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአውሮፕላን አደጋ ሕይወታቸውን ላጡት የመታሰቢያ ሐውልት ሊቆምላቸው መሆኑ ተነገረ፡፡

ከሁለት ዓመት በፊት በተከሰተው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአውሮፕላን አደጋ ሕይወታቸውን ላጡት ኢትዮጵያዊያን የመታሰቢያ ሐውልት ሊቆምላቸው መሆኑ ተነገረ፡፡የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን እንዳስታወቀችው ቦይንግ ኩባንያ ለተጎጂ ቤተሰቦች በሰጠው ድጋፍ መሰረት በኢትዮጵያ ጉዳት የደረሰባቸው 18 ሰዎች ቤተሰቦች አደጋው በደረሰበት ስፍራ ያሉ ነዋሪዎች ላደረጉት ሰብዊነት በስፍራው ሐውልት እንዲሰራ ፍቃድ መስጠታቸው ተነግሯል።በዚህም አደጋው የደረሰበት የግምቢቹ ወረዳ ቱሉፈራና አጎራባች ቀበሌዎች ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ፕሮጀክቶች ሊተገበሩ መሆኑ የተጠቆመ ሲሆን ሶስት ጥልቅ የውሃ ጉድጓዶች፣ እያንዳንዳቸው 5 ብሎክ ህንፃዎች ያላቸው ሁለት የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ አንድ ጤና ኬላ ግንባታና ሰባት ድልድዮች ይሰራሉ ተብሏል፡፡ በዚህም በጊምቢቹ ወረዳ 4 ቀበሌዎች የሚኖሩ 13 ሺህ 852 አባወራዎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተገልጿል።ከቦይንግ ኩባንያ በተገኘው 106 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የልማት ድርጅት አማካኝት ይከናወናል ብሎም በአንድ ዓመት ከስድስት ወር ይጠናቀቃል የተባለውን የፕሮጀክቶቹን ክንውን የሚቆጣጠር ከኦሮሚያ ክልልና ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የተውጣጣ ኮሚቴ መዋቀሩን በመጠቆምም ጉዳት የደረሰባቸው 18 ኢትዮጵያዊያን የመታሰቢያ ሐውልት አደጋው በደረሰበት ስፍራ ይቆምላቸዋል ተብሏል፡፡

ዘገባው የኢዜአ ነው፡፡