LatestNews

ኢትዮ ቴሌኮም የ4ጂ ኤል ቲ ኢ አገልግሎትን በምስራቅ ሪጅን ከተሞች አስጀምሬአለሁ ብሏል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም የ4ጂ ኤል ቲ ኢ አገልግሎትን ድሬዳዋ፣ አይሻና ጭሮ ከተሞችን ጨምሮ በአገራችን በምስራቅ ሪጅን ከተሞች አስጀምሬአለሁ ብሏል፡፡ የ4 ጂ ኤል ቲኢ አድቫንስድ አገልግሎቱን ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በሌሎች የክልል ከተሞች ላይ በማስፋፋት ላይ መሆኑን የሚገልጸው ኩባንያው አሁን አገልግሎቱን ያስጀመረባቸው ከተሞችም የማስፋፊያው አካል መሆናቸውን ጠቅሷል፡፡ በኢትዮጵያ 127 ዓመታትን አስቆትሬአለሁ ያለው ኢትዮ ቴሌኮም የ4 ጂ ኤል ቲኢ አገልግሎትን በክልል ከተሞች ላይ በማዳረስ ላይ ያለው ከአገልግሎት ጥራት ባሻገር አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ለማስተዋወቅ እንዲያግዝ መሆኑንም ጨምሮ አመልክቷል፡፡አገልግሎቱ ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የኢንተርኔት ዳታ አገልግሎት ለማግኘት የሚያስችል በመሆኑ ደንበኞቼ አገልግሎታቸውን ዲጂታላይዝ ለማድረግ ብሎም ምርታማነታቸውን ለማሳደግ ያግዛቸዋል ብሏል፡፡በተጨማሪም በቅርቡ ስራ የጀመረውን የቴሌ ብር አገልግሎት ለመጠቀም እንደሚያስችል ገልጿል::