EthiopiaNews

በመዲናዋ የ2018 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዛሬ መሰጠት ተጀመረ።

ዛሬ ሰኔ 11 እና ነገ ሰኔ 12 ቀን 2018 ዓ.ም የሚሰጠው የ2018 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በ201 የፈተና ጣቢያዎች መሰጠት ነው የተጀመረው፡፡

ከሌሎች የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ጋር በመሆን በዳግማዊ ብርሀን አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመገኘት የፈተናውን አጀማመር የተመለከቱት የከተማዋ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ ፈተናው ያለምንም እንከን እንዲጠናቀቅ ለማስቻል ልምድ ያላቸው የፈተና አስፈጻሚዎችን ከመመልመል ጀምሮ ሌሎች በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል፡፡

ከ86 ሺህ 7 መቶ በላይ የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናውን ለመውሰድ ተመዝግበው ዝግጅት ሲያደርጉ መቆየታቸውን የጠቆሙት የቢሮው ሃላፊ በሁሉም የፈተና ጣቢያዎች የፈተናውን ሂደት የሚከታተሉ አመራሮችን ጨምሮ የጸጥታ አካላትና የፈተና አስፈጻሚዎች መመደባቸውን አመላክተዋል።

ተማሪዎች ውጤታማ እንዲሆኑ በየትምህርት ቤቱ የማጠናከሪያ ትምህርት ከመሰጠቱ ባሻገር ደረጃውን የጠበቀ የሞዴል ፈተና እንዲወስዱ መደረጉን ገልጸው ፈተናው ከኩረጃ ነጻ እንዲሆን ለተማሪዎችና የፈተና አስፈጻሚዎች ኦረንቴሽን መሰጠቱንም አመላክተዋል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv