EthiopiaNews

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት 6.8 ቢሊየን ብር ያልተሰበሰበ  ቀረጥና ታክስ የገቢ ሂሳብ መኖሩን  አሳውቋል።

መስሪያ ቤቱ ይህንን ያሳወቀው 6ኛው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በ5ኛ ዓመት የስራ ዘመኑ 26ኛ መደበኛ ስብሰባውን  ዛሬ ባካሄደበት መድረክ ነው ።

ም/ቤቱ በስብሰባው የፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የፌዴራል መንግሥት መ/ቤቶች የ2017 በጀት ዓመት ሒሳብ የፋይናንሺያል፣ የሕጋዊነት እና የክዋኔ ኦዲት ሪፖርትን ያደመጠ ሲሆን ሪፖርቱን ያቀረቡት የፌዴራል ዋና ኦዲተር ወ/ሮ መሰረት ዳምጤ ካለፉት አመታት ጋር ሲነጻጸር የጥሬ ገንዘብ ጉድለት እየቀነሰ መምጣቱን እና ለዚህም የኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መጠቀም አስተዋጽኦ ማድረጉን ገልጸዋል።

የገቢ ሂሳብን በሚመለከት 6.8 ቢሊየን ብር ያልተሰበሰበ  ቀረጥና ታክስ የገቢ ሂሳብ መኖሩን የተናገሩት ዋና ኦዲተሯ ይህም በገቢ አሰባሰብ ላይ ያለውን ክፍተት እንደሚያሳይ ጠቁመው በቀጣይ ተገቢው ክትትልና ጥረት መደረግ እንዳለበት አሳስበዋል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv