EthiopiaNews

በቁጥጥር ስር የዋሉት 2 ተጠርጣሪዎች

የግንባታ ፈቃድ ለመስጠት 50ሺ ብር መደለያ የተቀበሉ ግለሰቦች በፖሊስ እጅ ከፍንጅ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

ግለሰቦቹ የወንጀል ድርጊቱን የፈፀሙት በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 8 አስተዳደር ህንፃ ውስጥ መሆኑን ፖሊስ ገልጿል።

ዘነበ ንጉሴ የተባለው ግለሠብ በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድ የህንፃ መጠቀሚያ ባለሙያ ሲሆን የግል ተበዳይ የግንባታ ፍቃድ ለማውጣት 100ሺ ብር ተጠይቀው በድርድር 50ሺ ብር ይዘው እንዲመጡ ተስማምተዋል።

የግል ተበዳይ የደረሰባቸውን በደል ለክፍለ ከተማው ፖሊስ የወንጀል መከላከል መምሪያ በሰጡት ጥቆማ ተጠርጣሪው በክትትል አባሎች ገንዘቡን ሲቀበል እጅ ከፍንጅ ተይዟል።

ከጉዳዩ ጋር ተሳትፎ የነበረው በክፍለ ከተማው የግንባታ ፈቃድ የመጠቀሚያ ፈቃድ ባለሙያ የሆነው አድምቀው ውቤ የተባለው ግለሰብ የግል ተበዳይን ጉቦ ካልከፈለ አገልግሎት እንደማይሰጠው በመንገርና ለአንድ ወር በማጉላላት 50ሺ ብሩን እንዲሰጥ በማድረግ የማግባባት ስራ ሲሰራ እንደነበር ፖሊስ ገልጿል።

ህብረተሰቡ መብቱን በገንዘብ መግዛት እንደሌለበት ያሳሰበው ፖሊስ መሠል የወንጀል ድርጊት ሲፈጸም ጉዳዩን በእጅ ስልኮች የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያ በመጠቀም መረጃ መስጠት እንደሚችልም ገልጿል፡፡መረጃው ከአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን የተገኘ ነው።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv