የኢንቬስተሮች ኤክስፖ
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን የመጀመሪያው የካፒታል ገበያ የኢንቬስተሮች ኤክስፖ የፊታችን ሰኔ 12 እና 13 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚካሄድ አስታወቀ።
ባለስልጣን መ/ቤቱ ኤክስፖው በአዲስ አበባ ባህልና ኪነጥበብ ቢሮ ግቢ እንደሚሄድ ገልጿል።
ይህ ኤክስፖ ሙሉ በሙሉ ለህዝብ ክፍት እንደሚሆን እና ለመታደምም የግድ መመዝገብ አያስፈልግም ተብሏል።
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ፣ የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ እና የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎችን ጨምሮ ዋና ዋና የገበያው ተዋናዮች በቀጥታ የሚገናኙበት መድረክ ነው ተብሏል።
የኤክስፖው ተሳታፊዎች የኢንቨስትመንት አካውንት ለመክፈት የሚችሉበት እድል መመቻቸቱም ነው የተገለፀው።መረጃው ከኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን የተገኘ ነው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
