የቁልፍ መሠረተ ልማቶች የሳይበር ደህንነት
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 24ኛ መደበኛ ስብሰባው የቁልፍ መሠረተ ልማቶች የሳይበር ደህንነት ረቂቅ አዋጅን መርምሮ በሙሉ አጽድቋል፡፡
ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳቡን ለምክር ቤቱ ያቀረበው የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሲሆን የሳይበር ደህንነት ፕሮግራሞችን ለማስፈጸም፣ ለሥልጠና፣ ለምርምርና ለቴክኖሎጂ አቅም ግንባታ የሚውል ራሱን የቻለ የቁልፍ መሠረተ ልማቶች የሳይበር ደህንነት ፈንድ በአዲስ ምዕራፍ መደንገጉንም አስረድቷል፡፡
በአዋጁ አፈጻጸምና በቅጣት አወሳሰድ ላይ በመንግሥትና በግል ተቋማት መካከል የነበረው ልዩነት ተሰርዞ አዋጁ በመንግሥትም ሆነ በግል ቁልፍ መሠረተ ልማቶች ላይ እኩልና ፍትሐዊ ተፈጻሚነት እንዲኖረው መድረጉም ተነግሯል፡፡
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
