በቡራዩ ከተማ በድብቅ ሲመረት የነበረና “ባትማን” የተባለ ስናክ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተነግሯል።

በቡራዩ ከተማ በድብቅ ሲመረት የነበረና “ባትማን” የተባለ ስናክ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተነግሯል።በህገወጥ መንገድ ንጽህና በጎደለው ቦታ ሲመረት የነበረ የምግብ ዘይትም በሱሉልታ ከተማ መያዙን የኢትዮጵያ የምግብና መድሀኒት ባለስልጣን በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል።ባለስልጣኑ ከክልሉ ጤና ቢሮ፣ከከተሞቹ ፖሊስና ከሌሎችም የሚመለከታቸው መስሪያ ቤቶች ጋር ባደረገው ክትትል የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸውና የት፣በማን፣በምንና መቼ እንደተመረቱ የማይታወቁና በ12 የዛጉ በርሜሎች የተከማቸ የዘይት ምርት እርምጃ እንዲወሰድበት ማድረጉን አስታውቋል።ከዚህም በተጨማሪ 39 ማዳበሪያ የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ካለፈባቸው ብስኩቶችና ምንነታቸው ከማይታወቁ ማጣፈጫዎች ተፈጭቶ የተዘጋጀ ባትማን የተባለ ብስኩት ወደገብያ ከመሰራጨቱ በፊት ተይዞ እርምጃ እንዲወሰድበት ማድረጉንና ህብረተሰቡም ካጋጠመው መጠቀም እንደሌለበት ያስጠነቀቀው ባለስልጣኑ መሰል ጉዳዮች ሲያጋጥሟችሁ በነጻ የስልክ መስመር 8482 አስታውቁኝ ብሏል።

Join Our Telegram

Click Here To follow Us