EthiopiaLatestNews

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ የመታወቂያ አሰጣጥ ስርዐትን በተመለከተ መመሪያ አውጥቷል።

የመመሪያው ዋና ዋና ሀሳቦችጊዜያዊ መታወቂያ እንዲወስዱ የማይገደዱ ሰዎች እና ስለ ጊዜያዊ መታወቂያ አሰጣጥ ስርዓት1. ጠቅላላ1) የነዋሪነት መታወቂያ፣ የመንጃ ፈቃድ፣ ፓስፖርት ወይም ከነዚህ ተመጣጣኝ የሆነ መታወቂያ ሰነድ ያለው ሰው ጊዜያዊ መታወቂያ እንዲያወጣ አይገደድም፡፡2) የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ፀንቶ በሚቆይበት ወቅት መደበኛ መታወቂያ ማውጣትን አስመልክቶ የሚጣሉ ገደቦች፣ ከልከላዎች ወይም የሚተላለፉ ትዕዛዞች የመታወቂያ እድሳት ላይም ተፈፃሚ ይሆናሉ። 2. ተመጣጣኝ መታወቂያ ሰነዶች የሚከተሉትን ሁኔታዎች ያሟሉ ሰዎች ተመጣጣኝ የሆነ መታወቂያ ሰነድ እንዳላቸው ተቆጥረው ጊዜያዊ መታወቂያ እንዲወሰዱ አይገደዱም፡1) በሚሰሩበት ተቋም ወይም ድርጅት የተሰጠ የሰራተኛነት መታወቂያ ያላቸው የመንግስት ሰራተኞች፣ ሕጋዊ ሰውነት ያለው የንግድ ድርጅት ሰራተኞች፣የመንግስት የልማት ድርጅት ሰራተኞች፣ ህጋዊ ሰውነት ያለው መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ሰራተኞች፣2) አግባብነት ካለው አካል የተሰጣቸው የማንነት መታወቂያ ያላቸው ስደተኞች፣ 3) ህጋዊ እውቅና ካለው የትምህርት ተቋም የተማሪነት መታወቂያ ያላቸው ተማሪዎች፡፡3. ስለ መስፈርቶችማንኛውም እድሜው 18 ዓመት የሞላው ሰው የሚከተሉትን መስፈርቶች ካሟላ ጊዜያዊ መታወቂያ እንዲሰጠው ማመልከት ይችላል፡-1. የአዲስ አበባ ነዋሪ ስለመሆኑ ህጋዊ የመኖሪያ መታወቂያ ያለው እና በአካባቢው ነዋሪነት የሚታወቅ የቤተሰብ ሃላፊ ስለአመልካቹ ማንነት እና ሰላማዊነት ሙሉ ሃላፊነቱን በመውሰድ ዋስ ሆኖ ለጊዜያዊ መታወቂያ የቀረበውን ማመልከቻ ከደገፈ፣ ወይም 2. አሁን ከሚኖርበት አካባቢ ውጪ ሌላ ቦታ ሲኖር የነበረ ሆኖ ከነበረበት ቦታ ሸኚ ወረቀት ማምጣት የሚችልና አሁን የሚኖርበት ቤት ህጋዊ ሰነድ ያለው ሆኖ የቤቱ ባለቤት ወይም ህጋዊ ወኪሉ ካስመዘገበው ወይም ዋስ ለመሆነ ፍቃደኛ ከሆነ፤3. በካምፕ፣ በማሰልጠኛ ወይም በአባላት የጋራ መኖሪያ ቤት የሚኖሩ የፖሊስ ሰራዊት ወይም የመከላከያ ሰራዊት አባላት ቤተሰባቸውና ራሳቸው በሚኖሩበት ቤት ቁጥር አገልግሎቱን እንዲያገኙ ከሚመለከተው አካል ተፈቅዶ ደብዳቤ ከተፃፈላቸው፣4. ጊዜያዊ መታወቂያ እንዲሰጥ ጥያቄ በቀረበበት አካባቢ ነዋሪ የሆነ ባለትዳር ባል ወይም ሚስት ከሌላ ቦታ በስራ ምክንያት የተዛወረ ከሆነና ስለመዘዋወሩ እና ህጋዊ ትዳር ስለመኖሩ በቂ ማስረጃ ካቀረበ፣4. የጊዜያዊ መታወቂያ የጊዜ ቆይታ እና ስለሚይዛቸው መረጀዎች 1. ጊዜያዊ መታወቂያ የሚሰጠው ለ6 ወር ሲሆን መታወቂያውን የያዘው ሰው በየወሩ መታወቂያውን የወሰደበት ቦታ በመቅረብ ሪፖርት ማድረግና ማሳደስ ይኖርበታል፣2. ጊዜያዊ መታወቂያ ላይ ግለሰቡ በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ የተነሳው ፎቶ የሚለጠፍ ሆኖ በመታወቂያው ላይ የሚሰፍሩ መረጃዎች ይዘት መደበኛው መታወቂያ የሚይዛቸው መረጃዎች ይሆናሉ::5. ጊዜያዊ መታውቂያ የመስጠት ሀላፊነት ያለባቸው አካላትየሚከተሉት አካላት ጊዜያዊ መታወቂያ የመስጠት ሀላፊነት አለባቸው፡-1) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላምና ፅጥታ መዋቅር፣ 2) በድሬዳዋ እና በክልሎች ደግሞ የፖሊስ መዋቅር፡፡6. ማንነትን ስለማረጋገጥጊዜያዊ መታወቂያ ለመውሰድ የሚያመለክት ማንኛውም ግለሰብ ስለትክክለኛ ማንነቱ መታወቂያውን በሚወስድበት ቦታ በመንግስት አካል በሚዘጋጅ ቅፅ ላይ የተመለከቱ ማንነትን ለማረጋገጥ የሚጠቅሙ መረጃዎችን በመሙላትና ቃለ መሀላ በመፈጸም ያረጋግጣል። 7. የጊዜያዊ መታወቂያ አገልግሎትበዚህ መመሪያ መሰረት የሚሰጥ ጊዜያዊ መታወቂያ መታወቂያውን የወሰደውን ሰው ማንነትን ከማረጋገጥ ውጪ መደበኛው የነዋሪነት መታወቂያ የሚያስገኛቸውን ጥቅሞች ወይም መብቶች አያስገኝም፡፡ግዴታዎችና የተከለከለ ተግባራት8. ማህበራዊ ጉዳይን የሚመለከት ተግባርና ሀላፊነት ያለባቸው የመንግስት ተቋማት ግዴታዎችማህበራዊ ጉዳይን በተመለከተ ሀላፊነት ያለባቸው የፌዴራልና የክልል የመንግስት ተቋማት ከሚመለከታቸው መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ አካላት ጋር በተባበር ጎዳና ተዳዳሪዎችን፣ ቋሚ አድራሻ እና ስራ የሌላቸውንና ሌሎች በተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን በማደራጀት ወደ መጠለያ ወይም ጊዜያዊ መቆያ እንዲገቡ እና በዚያ ቦታ እንዲቆዩ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡9. ጊዜያዊ መታወቂያ የወሰደ ሰው እና የመታወቂያ ሰጪው አካል ግዴታዎች1) ጊዜያዊ መታወቂያ የጠፋበት፣ የተበላሸበት ወይም በሌላ ምክንያት ጉዳት የደረሰበት ወይም በማናቸውም ምክንያት ከእጁ የወጣበት ማንኛውም ሰው ለፖሊስ በ24 ሰዓት ውስጥ ሪፖርት የማድረግ ሀላፊነት አለበት፣2) በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 1 የተመለከተው ሁኔታ ሪፖርት ፖሊስ ተቋም በሚሰጠው ማረጋገጫ መሰረት ጊዜያዊ መታወቂያ የመስጠት ስልጣን የተሰጠው አካል፣ ምትክ ጊዜያዊ መታወቂያ ይሰጣል::10. የተከለከሉ ተግባራትየሚከተሉትን ተግባራት መፈጸም በአዋጁ እና ሌሎች ህጎች መሰረት የወንጀል ኃላፊነት ያስከትላል፡-1) ጊዜያዊ መታወቂያ ለመውሰድ ሀሰተኛ መረጃ መስጠት ፣2) መስፈርቱን ለማያሟላ ሰው ጊዜያዊ መታወቂያ መስጠት፤3) መስፈርቱን የማያሟላ ሰው ጊዘያዊ መታወቂያ እንዲሰጠው በማሰብ ማረጋገጫ ደብዳቤ መፃፍ ወይም ምስክር መሆን፣4) ከአንድ በላይ ጊዜያዊ መታወቂያ ይዞ መገኘት፡፡ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች11. ተፈፃሚነት የሌላቸው መመሪያዎች ወይም ልማዳዊ አሰራሮችከዚህ መመሪያ ጋር የሚቃረን ማንኛዉም መመሪያ ወይም የአሰራር ልምድ በዚህ መመሪያ በተሸፈኑ ጉዳዮች ላይ ይህ መመረያ ጸንቶ በሚቆይበት ጊዜ ተፈፃሚነት አይኖረዉም፡፡ 12. መመሪያዉ የሚፀናበት ግዜ ይህ መመሪያ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ ከፀደቀበት ቀን ጀምሮ የሚጸና ሲሆን አዋጁ ጸንቶ በሚቆይበት ጊዜ ሁሉ በየትኛውም የኢትዮጵያ ከተማ ላይ ተፈፃሚነት ይኖረዋል፡፡