በኢትዮጵያ ያለው የወተት ፍላጎት እና ይህንን ለማቃለል የሚሰሩ ስራዎች

በኢትዮጵያ ያለው የወተት ፍላጎት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ ይነገራል ይህንን ለማቃለል የተለያዩ ስራዎች እየተከወኑ ቢሆንም አሁንም ግን በተለይ በአዲስ አበባ የሚኖሩ ዜጎች ወተት የሚያገኙት ከወተት አላቢ አርሶ አደሮች ነው መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከሆነ በኢትዮጵያ ለወተት አለመጨመር ምክንያቶች ማህበረሰብ አቀፍ የእንስሳት ጤና ባለሞያዎች በበቂ ደረጃ አለመኖር፣የእንስሳት መኖ አቅራቢዎች ቁጥር አነስተኛ መሆንና በቅጡ የተዘጋጀ የወተት ውጤቶች ማቅረቢያ መሰረተ ልማት አለመኖር በዋናነት ይጠቀሳሉ፡፡

የግብርና ሚኒስቴር ታድያ ይህንንና መሰል በዘርፉ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ከአጋር አካላቶች ጋር በመሆን “ስለ ወተት ዝም አንልም”የተባለ ዘመቻ መጀመሩን ሰምተናል፡፡ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰአት 7.1 ቢሊየን ሊትር ወተት በአመት እያመረተች እንደሆነ የሚናገረው ሚኒስቴሩ ይህንን ወደ 11 ቢሊየን ሊትር ለማሳደግ እቅድ መያዙንና በነፍስ ወከፍ አንድ ሰው ያገኝ የነበረውን 19 ሊትር የወተት መጠን ወደ 39 ሊትር እንደሚያሳድግ አስታውቋል፡፡

በአለም የጤና ድርጅት መስፈርት መሰረት አንድ ሰው በነፍስ ወከፍ 200 ሊትር ወተት ማግኘት አለበት እንደሚል ያስታወሰው ሚኒስቴሩ ከዚህ ካደጉት አገራት መጠን ጋር ለመስተካከል በአመት 22 ቢሊየን ሊትር ማምረት ይጠበቅብኛልና የሚመለከታችሁ አካላት በሙሉ ኃላፊነታችሁን በመወጣት፣የዝርያ ማሻሻያ ላይ በስፋት በመስራት፣መኖ በብዛት በማምረትና አርሶ አደሩን ከምርት ጀምሮ በማገዝ ልትተባበሩኝ ይገባል ብሏል፡፡

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 7696 ላይ ይላኩልን።

Join Our Telegram

Click Here To follow Us