EthiopiaLatestNews

ከበርካታ ሃገራት ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሱ ስደተኞች መካከል 77 በመቶው የሚሆኑት ከመካከለኛው ምሥራቅ ሀገራት መሆናቸው ተነገረ፡፡

በስደት ቆይተው በተለያየ ምክንያት ከበርካታ ሃገራት ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሱ ስደተኞች መካከል 77 በመቶው የሚሆኑት ከመካከለኛው ምሥራቅ ሀገራት መሆናቸው ተነገረ፡፡

ይህንን ያሉት ማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲና አለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት አይኦኤም አጥንቻለሁ ባሉት የዳሰሳ ጥናት ሲሆን ጥናቱ የ2013 ዓ.ም አገር አቀፍ የሰው ሃይልና ፍልሰት ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ቀርቧል፡፡

ጥናቱ ወቅታዊ የሰው ሃይል፧ የሥራ ሥምሪት፣ የአገር ውስጥ የስራ አጥና የስደት ተመላሾችን ሁኔታ የተመለከተ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን በመረጃ ላይ ተመስርቶ ውሳኔ ለመስጠት ያስችላል ተብሏል።

በክልሎች ላይ የተካሄደው ጥናቱ በአለም አቀፍ መመዘኛ መሠረት 49 ሺ 919 ቤተሰቦችን በናሙናነት መጠቀሙና ለሥራ ዝግጁ የሆነ የሰው ሃብት ምጣኔ፣ የሥራ አጥ ምጣኔ፣ ኮቪድ 19 ያደረሰው ጉዳትና የፍልሰተኞች ሁኔታ በጥናቱ ተመላክቷል።

ከተለያዩ አገራት ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሱ ስደተኞች መካከል 77 በመቶው ከመካከለኛው ምሥራቅ ፤13 በመቶ የሚሆኑ ከአፍሪካ አገራት፤ በሌላ በኩል ኮቪድ 19 ባስከተለው ጫና ደግሞ 44 በመቶ የሚጠጉ ቤተሰቦች ገቢያቸው መቀነሱን በጥናቱ ተገልጿል።

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 7696 ላይ ይላኩልን።

Join Our Telegram

Click Here To follow Us