InternationalLatestNews

ባይደን በየመን እየተካሄደ ለሚገኘው ጦርነት ድጋፋቸውን አቋረጡ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በየመን እየተካሄደ ለሚገኘው ጦርነት ድጋፋቸውን ማቋረጣቸው አስታውቀዋል፡፡

በየመን ለስድስት ዓመታት በዘለቀው ጦርነት ከ110 ሺህ በላይ ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡

ባይደንም በየመን የሚካሄደው ጦርነት መቆም አለበት ሲሉ አጽንዖት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡

አዲሱ ፕሬዚዳንት ይህንን ያሉት ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ በውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ዙሪያ ባደረጉት የመጀመሪያ ንግግር ነው፡፡

በየመን የሚካሄደው ጦርነት በሳዑዲ ዓረቢያ የሚመራው ጥምረት ከባይደን በፊት አሜሪካን ባስተዳደሩ ሁለት ፕሬዚዳንቶች ድጋፍ ይቸረው እንደነበር ይታወሳል፡፡

በአሁኑ ወቅት በሚሊየን የሚቆጠሩ የመናውያን ለረሃብ መጋለጣቸውን ዓለም አቀፍ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

ፕሬዚዳንቱ ባደረጉት የውጭ ፖሊሲ ንግግር ከየመን በተጨማሪ በስደተኞች ጉዳይ ላይም ትኩረት አድርገዋል፡፡

በዚህም ሃገራቸው የዶናልድ ትራምፕን ፖሊሲ በመቀልበስ በርካታ ስደተኞችን እንደምትቀበል ገልጸዋል፡፡

እንዲሁም ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጀምሮ በጀርመን የሰፈረው የአሜሪካ ጦር እንደሚያስወጡ አስታውቀዋል፡፡

በተጨማሪም የማይናማር ጦር የሃገሪቱን መሪ አሳን ሱ ኪን እንዲለቅና ደሞክራሲን እንዲያሰፍን ጥሪ አቅርበዋል፡፡