ትውልደ ኢትዮጵያዊው የአሜሪካ ሹመኛ
ትውልደ ኢትዮጵያዊው ዮሐንስ አብርሃም የካማላ ሀሪስ የፕሬዚዳንታዊ ሽግግር ቡድን ኃላፊ ሆነው ተመርጠዋል።
መቀመጫውን ጃካርታ ባደረገው የደቡብ ምስራቅ እስያ ሀገራት የአሜሪካ አምባሳደር ሆነው በማገልገል ላይ የሚገኙት ትውልደ ኢትዮጵያዊው አምባሳደር ዮሐንስ በቀጣይ ቀናት ወደ ዋሽንግተን በመመለስ ዴሞክራቶችን ወክለው በመጪው የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የሚፎካከሩት ካማላ ሀሪስ ፕሬዝዳንታዊ ሽግግር ቡድንን በኃላፊነት ይመራሉ መባሉን ከኤንቢሲ ኒውስ ተመልክተናል።