InternationalNews

አሜሪካና ኢራን በኒውክለርና የኢራን ሀብት ላይ ዳግም ውዝግብ ውስጥ መግባታቸው ተገለፀ።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቴህራን የኒውክለር ፕሮግራሟ ሳይቋረጥ እየተመረመረ እንዲቀጥል መስማማቷን ቢገልጹም ኢራን ይህ የፕሬዝዳንቱ ንግግር ፍፁም ሐሰት ነው ስትል አስተባብላለች፡፡

ሁለቱ ሀገራት በስዊዘርላንድ ካደረጉት የፊት ለፊት ንግግር በኋላ እንዳይንቀሳቀስ በታገደው የኢራን ሀብት ዙሪያም እርስ በርስ የሚጣረስ መግለጫ መስጠት መቀጠላቸውን ተከትሎ ሁለቱ ሀገራት የደረሱበት የመግባቢያ ስምምነት ላይ ጥያቄን አስነስቷል፡፡

ሆኖም ትላንትና በፔንሴልቬንያ ንግግር ያደረጉት ትራምፕ ሀገራቸው ከኢራን ጋር እያደረገች ያለችው ድርድር በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ነው የተናገሩት፡፡ ዘገባው የሮይተርስ ነው፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews