InternationalNews

በአሜሪካ በአንድ ፖሊስ ጥቃት ላይ ተሳትፈዋል የተባሉ 8 ግለሰቦች በ450 ዓመት እስራት ተቀጡ።

በአሜሪካ ቴክሳስ ግዛት በሚገኘው የስደተኞች እስር ቤት ፊት ለፊት በተከሰተ እና አንድ ፖሊስ ላይ ጥቃት እንዲፈጸም ባደረገው አመፅ ላይ ተሳትፈዋል የተባሉ 8 ግለሰቦች በአጠቃላይ በ450 ዓመታት እስራት መቀጣታቸው ተነገረ፡፡

ግለሰቦቹ አንቲፋ ከተባለው እና በአሜሪካ በሽብርተኝነት ከተፈረጀው ቡድን ጋር ግንኙነት አላቸው የተባለ ሲሆን ፍርደኞቹ በዴሞክራሲ ላይ ጥቃት ፈፅመዋል ተብለው ነው ከባዱ እስራት የተፈረደባቸው፡፡

በአመፁ ወቅት አንድ ፖሊስ በጥይት እንዲመታ እና ጉዳት እንዲደርስበት አድርጓል የተባለው ቀዳሚው ተከሳሽ 100 ዓመት ሲፈረድበት ሌሎቹ ደግሞ ከ30 እስከ 70 ዓመታት በሚደርስ እስራት ነው የተቀጡት፡፡

የአሜሪካ የፍትህ ሚኒስቴር ስለፍርዱ በሰጠው መግለጫ ፍርዱ የሀገሪቱ የፀጥታ ኃይሎችና የፌደራል ንብረቶች ላይ ጥቃት በማድረስ ለማምለጥ የሚሞክሩ የአንቲፋ ሽብር ቡድን አባላትን ያስተምራል ብሏል፡፡ ቢቢሲ እንደዘገበው፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews