EthiopiaInternationalNews

አሜሪካው የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ

የአሜሪካው የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሀመር ኢትዮጵያን ጨምሮ በቤልጅየምና ኬንያ የሥራ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ተነግሯል፡፡

መልዕክተኛው በቤልጄም ቆይታቸው በአፍሪካ ቀንድ እየተከሰቱ ያሉ ጉዳዮች ዙሪያ ከአውሮፓ ህብረት ጋር እንደሚመክሩ ሲገለጽ በኬንያ ደግሞ ቀጠናዊ እና የፀጥታ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክሩ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያወጣው መረጃ ያመለክታል፡፡

ማይክ ሐመር በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ ስለፕሪቶሪያው ስምምነት አተገባበር፣ እንዲሁም በአማራና ኦሮሚያ ክልል የቀጠሉትን ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ መፍታት በሚቻልበት ሁኔታንና ስለሱዳን ጉዳይ፣ ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሏል፡፡