አሜሪካ ለቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ
የገንዘብ ሚኒስቴር አሜሪካ ለቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ጠንካራ ድጋፍ መስጠቷን አስታወቀ።
ኢትዮጵያ ለአውሮፕላን ማረፊያው ፕሮጀክት የሚውል የገንዘብ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር በዋሽንግተን ዲሲ አካሂዳለች።
በመድረኩ ላይ ኢትዮጵያ ለቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ከአሜሪካ መንግሥት ተቋማት፣ ከታዋቂ የፋይናንስ ተቋማት እና ከዘርፉ ግዙፍ ኩባንያዎች ጠንካራ ድጋፍ አግኝታለች።
ድጋፉ በአፍሪካ ግዙፍ ከሆኑ የአቪዬሽን መሠረተ ልማቶች አንዱ የሆነውን ይህን ፕሮጀክት እውን ለማድረግ እንደሚያስችል የገንዘብ ሚኒስቴር ገልጿል።
የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ አውሮፕላን ማረፊያው ዓለም አቀፋዊ ፋይዳ ያለውና ቅድሚያ የሚሰጠው ሀገራዊ ፕሮጀክት መሆኑን ጠቅሰው፤ በዋሽንግተን የታየው ድጋፍ በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ መፃኢ ዕድል ላይ ያለውን እምነት የሚያንፀባርቅ መሆኑን አስረድተዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው ከአሜሪካ አጋሮች ጋር ያለው ትብብር ለአየር መንገዱ የስኬት መሠረት መሆኑን ጠቅሰው፣ ፕሮጀክቱ አዲስ አበባን ግንባር ቀደም የአቪዬሽን ማዕከል ለማድረግ እንደሚያስችል ገልጸዋል።
መረጃው ከገንዘብ ሚኒስቴር የተገኘ ነው።
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
