EthiopiaNews

የጦር መሣሪያዎች ምዝገባ

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በተቋሙ ግምጃ ቤትና በአባላቱ እጅ የሚገኙ የጦር መሣሪያዎች ላይ ምልክት የማድረግና ወደ ዘመናዊ የመረጃ ቋት የማስገባት ሥራ በይፋ መጀመሩን አስታውቋል።

ተቋሙ አዲሱ አሠራር በሀገር አቀፍ ደረጃ የትኛው የጦር መሣሪያ የት እንደሚገኝ በቀላሉ ለማወቅና ለመቆጣጠር ያስችላል ብሏል።

ተቋሙ ምልክት የማድረጉ ሥራ ሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውርን ለመግታት፣ የጠፉ መሣሪያዎችን ለመለየትና በጦር መሣሪያ የታገዙ ወንጀሎችን ለመመርመር ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር ገልጿል።

ተቋሙ የምዝገባ ሶፍትዌሩና የመረጃ ቋቱ በተቋሙ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ቡድን መበልፀጉን ገልፆ የጦር መሳሪያ ምዝገባው በቀጣይ በሁሉም ክልሎችና የከተማ አስተዳደር ፖሊስ ተቋማት ውስጥ ተግባራዊ እንደሚደረግ ገልጿል።

መረጃው ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የተገኘ ነው።

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv