EthiopiaNews

ዜና ሹመት

የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን 4 የተጓደሉ አመራሮች ተሾሙለት ።

የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 16ኛ መደበኛ ጉባኤ የተጓደሉ 4 የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን አመራሮችን ሹመት መርምሮ አፅድቋል።

ምክር ቤቱ በሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ለማሻሻል ባወጣው አዋጅ ቁጥር 1224/2012 አንቀፅ 2/6 መሰረት የተጓደሉ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽኖችን በመስፈርቱ መሰረት ምልመላ ሲያካሄድ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

በዚሁ መሰረት ሚዛኔ አባተ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ምክትል ዋና ኮሚሽነር፣ አሸነፈች አበበ የሴቶችና ህፃናት ጉዳዮች ዘርፍ ኮሚሽነር ፤ መሃመድ አህመድ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የአካል ጉዳተኞችና አረጋዊያን ጉዳዮች ዘርፍ ኮሚሽነር እንዲሁም በዳሳ ለሜሳ የትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ኮሚሽነር አድርጎ ምክር ቤቱ በአንድ ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል።

መረጃው ከህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የተገኘ ነው።

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv