የኢራን ጦርነት ማብቂያ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለኢራን ጦርነት ማብቂያ የተቀመጠ የጊዜ ሰሌዳ የለም አሉ።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለፎክስ ኒውስ እንደተናገሩት ኢራንን በተመለከተ ለእኛ የሚስማማ ስምምነት እስኪደረስ ድረስ ጦርነቱ ሊቀጥል ይችላል ብለዋል።
የዋይት ሀውሷ ቃል አቀባይ ካሮሊን ሌቪት በፊናቸው ፕሬዝዳንቱ ለኢራን የማይታለፈውን ቀይ መስመር አስቀምጠዋል፤ እሱም ኢራን በእጇ ያለውንና ኒውክለር ለመስራት ያብላላችውን ዩራኒየም ሁሉ ለአሜሪካ ማስረከብ ነው ብለዋል። ቃል አቀባይዋ አክለውም በዚሁ ዙሪያና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ከኢራን ጋር ድርድሩ እንደቀጠለ ነው ብለዋል።
በሌላ በኩል ኢራን የኒውክለር መስሪያ ዩራኒየሙን ለአሜሪካም ሆነ ለሌላ ሦስተኛ ወገን መቼም አሳልፋ እንደማትሰጥ እየገለፀች ነው።
በአሜሪካ የተጣለባት የመርከቦች ዝውውር እገዳ ሳይነሳም የሆርሙዝ ሰርጥ ፈፅሞ አይከፈትም እያለችም ነው።
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
