አትሌት ሰለሞን ባረጋ በቶኪዮ ኦሊምፒክ የወንዶች 10 ሺህ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ አሸነፈ

አትሌት ሰለሞን ባረጋ በቶኪዮ ኦሊምፒክ የወንዶች 10 ሺህ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ አሸንፏል።በቶኪዮ ኦሊምፒክ ዛሬ በተደረገው የወንዶች 10 ሺህ ሜትር ፍፃሜ ውድድር አትሌት ሰለሞን ባረጋ አንደኛ በመውጣት በኦሊምፕኩ ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ወርቅ አስገኝቷል።