EthiopiaLatestNews

ሰሞኑን የሚታየው ዝናባማ እና ጭጋጋማ አየር ከአየር ትንበያው አንጻር የሚጠበቅ መሆኑን ተገለጸ፡፡

ብሔራዊ ሜትሮሎጂ ኤጀንሲ ሰሞኑን የሚታየው ዝናባማ እና ጭጋጋማ አየር ከአየር ትንበያው አንጻር የሚጠበቅ መሆኑን አስታውቋል።

ይህን ተከትሎም በሃገሪቱ ላይ መደበኛና ከመደበኛ በላይ የሆነ ዝናብ ሊመዘገብ እንደሚችል ኤጀንሲው በትንበያው ማመላከቱን ተከትሎ በጭጋጋማው አየር የሚከሰተው የእይታ መጋረድ ጉዳት እንዳያስከትል ተገቢውን ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበትም ተናግሯል።
ይህ የአየር ንብረት በኢትዮጵያ ለአጭር ጊዜ በሐምሌና በነሐሴ ወራት የሚታይ ሲሆን የአየር ሁኔታው ዘላቂነት እንደማይኖረውም ተገልጿል።

በተጨማሪም ኤጀንሲው ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕና ከኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ጋር በቅንጅት በመስራት ጭጋጋማው አየር ከአየር ትራንስፖርት ጋር የሚኖረውን ተጽእኖ አስመልክቶ ዕለታዊ መረጃዎችን ለራሳቸው ለተቋሟቱ እየሰጠ እንደሆነም ገልጿል ።