አዋሽ ባንክ በቀጣይ ዓመት ከኢትዮጵያ ውጭ ባሉ ጎረቤት ሀገራት ቅርጫፎችን ከፍቶ ለመሥራት በሂደት ላይ ነው ተባለ።
አዋሽ ባንክ በቀጣይ ዓመት ከኢትዮጵያ ውጭ ባሉ ጎረቤት ሀገራት ቅርጫፎችን ከፍቶ ለመሥራት ለብሔራዊ ባንክ ጥያቄ አቅርቦ ፈቃድ እስኪያገኝ እየተጠባበቀ እንደሚገኝም አስታውቋል።
ባንኩ ይሄን ያለው የ2025 /2026 ዓመት አፈጻጸም አስመልክቶ ትንናንት በሰጠው መግለጫ ላይ ነው።
የውጭ ምንዛሬ ግኝትን በተመለከተ ባንኩ በበጀት ዓመቱ ከ2 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር በላይ መሰብሰቡ የተገለጸ ሲሆን ይህም ከቀደመው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ635 ሚሊዮን ዶላር ጭማሪ የተመዘገበበት ነው ተብሏል፡፡
ባንኩ በበጀት ዓመቱ የሰጠው ብድር ወደ 53 ቢሊዮን ያደገበትና በዲጂታል አመራጭን ጨምሮ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ለሆኑ ዜጎች ብድር ያቀረበበት ዓመት መሆኑን ገልጿል፡፡
የባንኩ ጠቅላላ ተቀማጭ ከ467 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱ ተገልጿል።
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
