EthiopiaNews

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ የሀገር ውስጥ ምርትን በራስ አቅም መሸፈን የኢኮኖሚ ሉዓላዊነታችን መሰረት ነው አሉ፡፡

በጋሞ ዞን ነሐሴ 2017 ዓ.ም ሥራ የጀመረው ‘ዮ ሆልዲንግ’ የድንጋይ ከሰል ፋብሪካ፤ የኢንዱስትሪዎችን ፍላጎት በሀገር ውስጥ በመተካት ከውጭ የሚገባ ምርት ማስቀረት መቻሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የድንጋይ ከሰል ፋብሪካውን በጎበኙበት ወቅት ለአካባቢው ነዋሪዎች የሥራ ዕድል መፍጠሩን ጠቅሰው፤ የተፈጥሮ ሀብታችንን በማልማት የኢኮኖሚ ልዕልናችንን የምናረጋግጥበት ጉዞ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሚገኘውና የገጠር ኮሪደር ልማት አካል የሆነው የሀማሳ ሞዴል መንደር በዛሬው ዕለት መርቀዋል፡፡ ‎

መንደሩ በ79 ነጥብ 4 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን የአርሶ አደሩን ኑሮና ምርታማነት ለማሳደግ የሚያግዙ ዘመናዊ የመታጠቢያ ክፍሎች፣ የእንስሳት ማደሪያ፣ የአትክልት ስፍራ፣ የባዮ ጋዝ እና የንብ ቀፎዎች የተሟሉለት መሆኑም ተነግሯል፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews