በኢትዮጵያ እና በኬንያ ድንበር የሚደረግ ንግድ በወር ከ1 ሺህ የአሜሪካ ዶላር እንዳይበለጥ የሚያዝ መመሪያ ተግባራዊ ተደርጓል፡፡
ይህ አዲስ አሰራር በኢትዮጵያና በኬንያ ድንበር የሚከናወነውን የንግድ ልውውጥ ህጋዊ ለማድረግ የሚያስችል መሆኑንም የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በመመሪያው ላይ አስፍሯል፡፡
ይህ የሁለቱ ሀገራት የጠረፍ ንግድ መመሪያ በድንበር አካባቢ የሚኖሩ ማህበረሰቦች መሰረታዊ የፍጆታ ዕቃዎችን በህጋዊ መንገድ እንዲያገኙ ለማስቻልና ከሀገሪቱ ዋና የንግድ ማዕከላት ርቀው ለሚኖሩ ነዋሪዎች የሚፈጠረውን የምርት እጥረት ለመቅረፍ ያለመ መሆኑም ተገልጿል፡፡
በዚህም መመሪያ ላይ ነጋዴው በወር የሚገበያይባቸው ዕቃዎች ጠቅላላ ዋጋ ከ1 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ወይም በወቅቱ ምንዛሪ ከ155 ሺህ ብር መብለጥ እንደሌለበት እንዲሁም ነጋዴዎች በወር አራት ጊዜ ብቻ በተገደቡ ምርቶች ላይ የድንበር ተሻጋሪ ንግድ ማካሄድ እንደሚችሉም ተደንግጓል።
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
