InternationalNews

አዲሱ የሩሲያ ሚሳኤል

🔸ሩሲያ እጅግ ዘመናዊ ነው የተባለ አህጉር አቋራጭ ሚሳኤል ሙከራ አካሄደች።

🔸የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እንዳሉት አር ኤስ 28 ሳርማት የተባለው ይህ ሚሳኤል የትኛውንም የፀረ ሚሳኤል ስርዓት ጥሶ የመግባት አቅም ያለው ነው።

🔸የሩሲያ ጦር የስትራቴጂክ ሚሳኤል ወታደራዊ ምድብ አዛዥ ጀነራል ሰርጌይ ካርኪዬቭ አገራቸው የተሳካ የአህጉር አቋራጩን ሚሳኤል ሙከራ ማካሄዷን ለፕሬዝዳንት ፑቲን ሪፖርት አድርገዋል።

🔸የሩሲያ ጦርም ይሄን ዘመናዊ ሚሳኤል በያዝነው የፈረንጆች ዓመት መጨረሻ ላይ ይታጠቀዋል ተብሏል።

🔸አዲሱ የሩሲያ ሚሳኤል አስር የሚደርሱ አረሮችን የመሸከም አቅም ያለው ሲሆን ከዚህ በላይ የመምታት አቅም ያላቸውን ቁሳቁሶችን ያካተተ ነው።

🔸ሚሳኤሉ በመሸከም አቅሙና በሚሸፍነው ርቀትም ቀድሞ ከነበሩት ሚሳኤሎች ብልጫ ያለው መሆኑ ተመልክቷል።

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews