EthiopiaNews

አዲሱ የቪዛ የክፍያ ካርድ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ ዓለም አቀፍ የቪዛ የክፍያ ካርድ ይፋ አደረጉ።

አዲሱ የቪዛ ዓለም አቀፍ የክፍያ ካርድ ትናንት ማምሻውን በስካይ ላይት ሆቴል በተዘጋጀ መርሀ ግብር ላይ ይፋ መደረጉን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገልጿል።

ሁለቱ ድርጅቶች ከቪዛ ኩባንያ ጋር በመተባበር ይፋ ያደረጉት የክፍያ ካርድ ደንበኞች በውጭ ሀገራት ቆይታቸው በቀላሉ ክፍያ እንዲፈጽሙ የሚያስችል ነው ተብሏል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሼባ ማይልስ አባላት የሆኑ መንገደኞች በሚደርሱበት ማንኛውም የዓለም መዳረሻ ካርዱን በሽያጭ መፈጸሚያ ማሽን ወይም ለኦንላይን ግብይት በሚጠቀሙበት ጊዜ ተጨማሪ የጉዞ ማይል ሽልማት እንደሚያስገኝላቸው ተገልጿል፡፡ መረጃው ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተገኘ ነው።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv