አዲስ ነገር – በኢትዮጵያ 1 ሚሊዮን ዶላር እና ከዛ በላይ ያካበቱ ባለሀብቶች

ኢትዮጵያ በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ያካበቱ ባለሀብቶች ከሚገኙባቸው 10 የአፍሪካ ሀገራት መካከል 7ኛዋ ሀገር ሀገር መሆን ችላለች።
አፍሪካ ቢዝነስ ኢንሳይደር የአውሮፓዊያኑ 2022 ኒው አፍሪካ ዌንዝ ሪፖርትን ዋቢ በማድረግ በአፍሪካ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዶላር ያካበቱ ሀገራትን ደረጃ አውጥቷል።
በወጣው ሪፖርት መሰረትም 7ኛ ደረጃ የያዘችው ሀገራችን ኢትዮጵያ 2ሺህ 900 የሚደርሱ የግል ባለሀብቶቿ የተጣራ 1 ሚሊዮን ዶላር ያካበቱ ስለመሆናቸው፣ 140 የሚደርሱት ደግሞ ከ1 ሚሊዮን ዶላር በላይ ያላቸው ስለመሆናቸው ተገልጿል። በዚህም አጠቃላይ በኢትዮጵያ የግል ሴክተር ብቻ 52 ቢሊዮን ዶላር ሀብት ስለመገኘቱ ነው ሪፖርቱ ያመለከተው።
በወጣው ዝርዝር መሰረት አንደኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው ደቡብ አፍሪካ ከ39 ሺህ በላይ የግል ባልሀብቶቿ ከአንድ ሚሊዮን ዶላር በላይ ያካበቱ ሲሆን ከ2 ሺህ በላይ ያሉትም የበርካታ ሚሊዮንና ቢሊዮን ዶላር ባለቤት ናቸው ተብሏል።
ከደቡብ አፍሪካ በመቀጠል ግብጽ፣ ናይጄሪያ፣ ኬንያና ሞሮኮ በቅደም ተከተላቸው የሚሊዮን ዶላር ባለቤትነት ተርታን የያዙ ሲሆን አጠቃላይ የአውሮፓዊያኑ 2022 የአፍሪካ የግል ሴክተሩ ሀብትም 2 ነጥብ 1 ትሪሊዮን መሆኑንና ይሄም ቁጥር በሚመጡት አስርት አመታት በ38 በመቶ እንደሚያድግ ተተንብዩዋል።