አዲስ ነገር – የምልክት ቋንቋ የስራ ቋንቋ

በኢትዮጵያ ተጨማሪ ቋንቋዎችን በሥራ ቋንቋነት ለማካተት የሚያስችል የቋንቋ ፖሊሲ በቀረጻ ላይ ቢሆንም መስማት ለተሳናቸው ሰዎች ግን የምልክት ቋንቋን የሥራ ቋንቋ ለማድረግ በቂ ትኩረት አለማግኘቱን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ገለጸ፡፡
ኮሚሽኑ በማህበራዊ የትስስር ገጹ እንደገለጸው የምልክት ቋንቋ ትኩረት የተነፈገው በመሆኑ መስማት የተሳናቸው ዜጎች ከማኅበራዊ ግንኙነቶች መገለልን ጨምሮ በመሰረታዊ አገልግሎቶችና በሥራ ዕድሎች ተደራሽነት ላይ እክል እያጋጠማቸው ነው ብሏል፡፡
በአንጻራዊነት በኢትዮጵያ የምልክት ቋንቋን የመጠቀም ልምድ በተወሰኑ ስብሰባዎች፣ ሕዝባዊ ዝግጅቶችና የቴሌቭዥን ጣቢያዎች ቀስ በቀስ እየታየ የመጣ ቢሆንም አስፈላጊው የሕግና የፖሊሲ ማዕቀፍ ባለመኖሩ ግን ሊያድግ እንዳልቻለም ኮሚሽኑ አመልክቷል፡፡
ስለሆነም የምልክት ቋንቋን በሥራ ቋንቋነት የሚደነግግና የሚያስተገብር የሕግና የፖሊሲ ማዕቀፍ እንዲሁም የአፈጻጸም ስትራቴጂዎች እንደሚያስፈለጉ ጠቁሞ የምልክት ቋንቋን ከሕግ አውጪ ምክር ቤቶች ጀምሮ በልዩ ልዩ ሕዝባዊ አገልግሎት መስጫዎች፣ በትምህርት ቤቶች፣ በመገናኛ ብዙኃንና በሌሎችም ዘርፎች እንዲስፋፋ ማድረግ ያሻል ብሏል፡፡

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New