News

አዲስ ነገር – የሱዳን ተፈላሚ ኃይሎች ሌላ አዲስ ለ7 ቀናት የሚፀና የተኩስ ማቆም ለማድረግ ከስምምነት መድረሳቸውን ደቡብ ሱዳን አስታወቀች ።

የሱዳን ተፈላሚ ኃይሎች ሌላ አዲስ ለ7 ቀናት የሚፀና የተኩስ ማቆም ለማድረግ ከስምምነት መድረሳቸውን ደቡብ ሱዳን አስታወቀች ።
የደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሱዳን የጦር መሪዎች ለ 7 ቀናት የሚዘልቅ የተኩስ አቁም ለማድረግ መስማማታቸውን ገልፆ በቀጣይ በደቡብ ሱዳን ለሚመራው የሰላም ድርድር ተፈላሚዎቹ መልዕክተኞች ይልካሉ ብሎ ተስፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል።
በሱዳን ውጊያ የሞቱ ሰዎች 550 ሲደርስ 5ሺ ያክል መቁሰላቸውን የሱዳን የጤና ሚኒስቴር ገልጿል።
በተያያዘ ዜና የግብፅ ፕሬዝዳንት አብደል ፈታ አል ሲሲ የሱዳን የጦር መሪዎችን ለማሸማገል እየሞከሩ እንደሆነ ተሰምቷል፡፡
ዘገባው የሚድል ኢስት ሞኒተር ነው፡፡
🇮🇷#ኢራን
የኢራኑ ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ራይሲ በሶሪያ ታሪካዊ ገብኝታቸውን መጀመራቸው ተሰምቷል፡፡
ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ራይሲ በ10 አመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በሶሪያ ባካሄዱት ጉብኝት ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት በሽር አል አሳድ ጋር በሁለትዮሽ እና በቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የኢራኑ መሪ ኢብራሂም ለሁለት ቀናት በሶርያ የጀመሩት ጉብኝት የቴህራን እና ደማስቆ ስትራቴጂካዊ ግንኙነት እየሰመረ መምጣቱን ማሳያ ነው ተብሎለታል፡፡
ኢራን ከሶሪያ ጋር ያላት የንግድ ፣ ዲፕሎማሲ እና ፖሊቲካዊ ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የቴህራን መንግስት ይሰራል ሲሉ የኢራን ባለስልጣናት ይገልጻሉ።
ዘገባው የአልጀዚራ ነው፡፡
#የመንግስታቱ ድርጅት
የመንግስታቱ ድርጅት በመላው ዓለም ለከፋ የምግብ እጥረት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር 258 ሚሊዮን ያህል መሆኑን አስታወቀ፡፡
ተመድ በአየር ንብረት ለውጥ ችግሮች፣ በግጭቶች ፣ እና በኮሮና ወረርሽኝ አሉታዊ ተፅዕኖዎች ባለፈዉ የአውሮፓውያኑ 2022፣ በ58 ሀገራት ለከፋ የምግብ እጥረት የተጋለጡ ሰዎች ቁጥር 258 ሚሊዮን ያክል መሆኑን ገልጧል።
የተመድ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በበኩላቸው የድህነት መስፋፋት፣ የገቢ አለመመጣጠን ችግሮች እና የተበራከቱ የተፈጥሮ አደጋዎች በዓለም ላይ የድጋፍ ፈላጊ ሰዎች ቁጥር እንዲያሻቅብ ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡
ዘገባው የአልጀዚራ ነው።
🇸🇴#ሶማሊያ
ሶማሊያ ከ50 አመታት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የሕዝብ እና ቤት ቆጠራ ማስጀመሯ ተነገረ።
በሶማሊያ ለሚካሄደው የሕዝብ እና ቤት ቆጠራ 30ሺ መረጃ ሰብሳቢ ሰራተኞች እንደሚሳተፉ ሲነገር የህዝብ እና ቤት ቆጠራው ሁለት አመታት እንደሚፈጅ ነው የሀገሪቱ መንግስት ያስታወቀው ።
የሶማሊያ የህዝብ እና ቤት ቆጠራ ቢሮ ኃላፊ አብዲ አሊ የህዝብ እና ቤት ቆጠራው ሂደት በመጀመሪያ በከተሞች ቀጥሎ በገጠራማ ግዛቶች የሚደረግ መሆኑን እና ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ጥቅም ላይ እንደሚውሉ ነው የተናገሩት፡፡
ዘገባው የአሜሪካ ድምጽ ነው፡፡

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New