News

አዲስ ነገር – ቮልከር ፐርዝስ የሱዳን ተፈላሚ ኃይሎች ድርድር ለመጀመር መስማማታቸውን አስታወቁ።

🇸🇩#ሱዳን
የመንግስታቱ ድርጅት በሱዳን ልዩ መልዕክተኛ ቮልከር ፐርዝስ የሱዳን ተፈላሚ ኃይሎች ድርድር ለመጀመር መስማማታቸውን አስታወቁ።
መልዕክተኛው ሁለቱ ተፋላሚ ኃይላት በሳዑዲ አረቢያ ለሚካሄደው ድርድር ተወካዮቻቸውን ለመላክ መስማማታቸውን ነው የተናገሩት።
ቮልከር ፐርዝስ አሁን በሱዳን ካለው ፈታኝ ሁኔታ አንጻር የሳኡዲ አረቢያው ድርድር ተጠባቂ ቢሆንም ሙሉ በሙሉ ይሳካል ብሎ ለመደምደም አስቸጋሪ ነው ብለዋል።
ዘገባው የአሶሼትድ ፕሬስ ነው።


የመንግስታቱ ድርጅት በሱዳን ለ18 ተከታታይ ቀናት ተባብሶ በቀጠለው ውጊያ 8 መቶ ሺ ሰዎች ከሀገሪቱ ሊሰደዱ ይችላሉ ሲል አስጠንቅቋል።
የሱዳን ተፋላሚ ሀይላት ትንናት ለሁለተኛ ጊዜ ለ72 ሰአታት የሚዘልቅ የተኩስ አቁም ለማድረግ ቢስማሙም በመላ ሀገሪቱ ውጊያው መቀጠሉን መቀጠሉ ነው የተነገረው፡፡
በሌላ በኩል የዓለም የምግብ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ሲንዲ ማኬይን በሱዳን ተቋርጦ የነበረው የድጋፍ ፕሮግራም መልሶ እንደሚቀጥል በይፋዊ የትዊተር ገፃቸው ይፋ አድርገዋል፡፡
ዘገባው የሬውተርስ ነው፡፡
🇺🇸#አሜሪካ
በቀጠለው የሩሲያ – ዩክሬን ጦርነት በ5 ወራት ውስጥ ብቻ ከ20ሺ በላይ የሩሲያ ወታደሮች መገደላቸውን አሜሪካ አስታወቀች፡፡
የአሜሪካ የብሔራዊ ደህንነት ቃል አቀባይ ጆን ኪርቢ በጦርነቱ ከተገደሉት ሺዎች ባሻገር የሩሲያ ወታደሮች 80 ሺ ወታደሮች መጎዳታቸው ነው የተገለጸው።
ዘገባው የቢቢሲ ነው፡፡
🇨🇳#ቻይና
ቻይና የመንግስታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ላይ ማሻሻያ እንዲደረግ ጥሪዋን አቀረበች ።
የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዩ አዳጊ በተለይም የአፍሪካ ሀገራት በፀጥታው ምክር ቤት በተገቢው ሁኔታ እንዲወከሉ ሲባል የፀጥታው ም/ቤት ላይ ማሻሻያ እንዲደረግ ነው ጥሪያቸውን ያቀረቡት ።
የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከኩዌት እና ኦስትሪያ ዲፕሎማቶች ጋር ባደረጉት ውይይት አዳጊ አገራት በፀጥታው ም/ቤት የውሳኔ ሰጪነት ሚና እንዲኖራቸው ም/ቤቱ መዋቅራዊ ማሻሻያ ሊያደርግ ይገባል ብለዋል።
በተያያዘ የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ እና በተመድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ ግሪን ፊልድ የፀጥታው ም/ቤት ማሻሻያ እንዲካሄድበት ድጋፍ ሰጥተዋል፡፡
ዘገባው የሩሲያ ቱዴይ ነው፡፡


በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች የደራ ግብይት ከሚካሄድባቸው ሀገራት ዝርዝር ውስጥ ቻይና የቀዳሚውን ደረጃ መያዟ ተሰማ፡፡
የዓለም አቀፉ የኢነርጂ ኤጀንሲ በአውሮፓውያኑ 2022 በመላው ዓለም ከተሸጡ 10 ሚሊዮን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ውስጥ 60 ከመቶው ሽያጭ የተካሄደው በቻይና መሆኑን አስታውቋል ።
የቻይናው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች አምራች ቢዋይዲ ኩባንያ በተያዘው የአውሮፓውያኑ 2023 ሩብ ዓመት ብቻ ትርፉ በ 411በመቶ ማደጉን ነው የተሰማው፡፡
በዚህ ዘርፍ አውሮፓ በሁለተኛ ደረጃ ስትቀመጥ አሜሪካ ደግሞ የ3ኛነት ደረጃ መቆናጠጧ ተነግሯል፡፡
ዘገባው የሩሲያ ቱዴይ ነው፡፡
ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New