አዲስ ነገር – የመንግስታቱ ድርጅት በሱዳን ግጭት ምክንያት 100 ሺ ዜጐች ከሀገሪቱ ሊሰደዱ ይችላሉ ሲል አስጠነቀቀ።
🇸🇩#ሱዳን
የመንግስታቱ ድርጅት በሱዳን ግጭት ምክንያት 100 ሺ ዜጐች ከሀገሪቱ ሊሰደዱ ይችላሉ ሲል አስጠነቀቀ።
የመንግስታቱ ድርጅት በሱዳን የቀጠለውን ግጭት ተከትሎ 20ሺ ሱዳናዊያን ቻድ መግባታቸውን ገልፆ የሱዳን የእርስበርስ ጦርነት የማይቆም ከሆነ አንድ መቶ ሺ ዜጐች ከሱዳን ወደ ቻድ ሊሰደዱ ይችላል ሲል ነው ይፋ ያደረገው፡፡
የተባበሩት መንግስታት በቻድ የተጠለሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችን ለመደገፍ ለጋሽ ሀገራት እገዛ እንዲያደርጉ መጠይቁ ተገልጿል፡፡
ዘገባው የአልጄዚራ ነው።
የዓለም የጤና ድርጅት በሱዳን በአብዛኞቹ የጤና ተቋማት አገልግሎቶች በመስተጓጎላቸው ምክንያት በርካታ ዜጐች ሳይሞቱ እንዳልቀረ ሥጋቱን ገልጿል።
የጤና ተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በሱዳን የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ በተቋረጡት የህክምና አገልግሎቶች ፣ የምግብ እና ሌሎች የነፍስ አድን ጥረቶች ሳቢያ በርካታ ሰዎች ለሞት ሳይዳረጉ እንዳልቀረ ነው በፅህፈት ቤታቸው በሰጡት መግለጫ የተናገሩት፡፡
ዶ/ር ቴድሮስ አክለውም በሱዳን መዲና ካርቱም ካሉ የጤና ተቋማት ውስጥ 16 ከመቶ ብቻ አገልግሎት እየሰጡ መሆናቸው ነው የተናገሩት፡፡
በሱዳን ግጭት 512 ሰዎች ሲሞቱ ከ4ሺ 1 መቶ የሚበልጡ ሱዳናውያን መጐዳታቸው ተነግሯል፡፡
ዘገባው የዩኤስ ኒውስ ነው፡፡
#የአፍሪካ ቀንድ ድርቅ
በአፍሪካ ቀንድ አገራት ያጋጠመው አስከፊው ድርቅ በዓለም የሙቀት መጨመር መከሰቱን አንድ የጥናት ግኝት ሪፖርት አመለከተ።
የዓለም አቀፍ የሳይንቲስቶች ቡድን የአየር ንብረት ለውጥ በምስራቅ አፍሪካ የተከሰተውን ድርቅ በመቶ እጥፍ እንዲጨምር አድርጓል ሲል ነው ባወጣው የጥናት ሪፖርት ይፋ ያደረገው፡፡
አጥኚው ቡድን በድርቅ የተጐዱትን ኢትዮጵያ ፣ ኬንያ እና ሶማሊያ ባካተተበት የጥናት ሪፖርቱ ከኢንዱስትሪዎች የሚለቀቀው የበካይ ጋዝ በቀጣናው ድርቅ እንዲከስት አድርጓል ሲል ነው ግኝቱን ያስታወቀው፡፡
የአየር ንብረት ለውጡ በዝናባማ ወቅቶች ፀሀያማ አየር፣ በፀሀያማ ወቅቶች ደግሞ ዝናባማ አየር እንዲከሰት በማድረግ በቀጣናው የወቅቶች መዘበራረቅን አስከትሏል ይላል የጥናቱ ግኝት፡፡
ዘገባው የኤ ኤፍ ፒ ነው።
🇨🇳#ቻይና
ቻይና የሩሲያ – ዩክሬን ጦርነት እንዲቆም የአደራዳሪነት ሚናዋን መወጣት መጀመሯ ተነገረ ።
የቻይናው ፕሬዚዳንት ዢ ጂን ፒንግ ከዩክሬኑ አቻቸው ቮሎዲሚር ዜሌኒስኪ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ባደረጉት ዘለግ ያለ የስልክ ውይይት ቤጂንግ የሩሲያ – ዩክሬን ጦርነት እንዲቆም የሚያደራድር ልዩ መልዕክተኛ ወደ ዩክሬን እንደምትልክ ለፕሬዚዳንት ዜሌንስኪ ነግረዋቸዋል።
ፕሬዚዳንት ዢ የቻይናው ልዩ መልዕክተኛ ጦርነቱ እንዲቆም እና የሰላም ስምምነቱ እንዲፈረም ለማስቻል በዩክሬን እና በተለያዩ ሀገራት የማደራደር ሥራቸውን ይጀምራሉ ብለዋል ።
ዘገባው የአሶሼትድ ፕሬስ ነው።
ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ
👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30
👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)
👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00
ዘወትር ቅዳሜ
👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት
ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።
አዲስ ነገር / What’s New