News

አዲስ ነገር – በሱዳን የተባባሰውን ግጭት

🇸🇩 #ሱዳን
የዓለም የጤና ድርጅት ለ10 ተከታታይ ቀናት በመላ ሱዳን በቀጠለው ውጊያ ከ420 የሚበልጡ ሰዎች መሞታቸውን እና 3ሺ 7 መቶ የሚሆኑ መቁሰላቸውን አዲስ ባወጣው ሪፖርቱ ይፋ አደረገ ።


በሱዳን የተባባሰውን ግጭት ተከትሎ በርካታ ሀገራት ዜጐቻቸውን ከሃገሪቱ ለማውጣት እየተረባረቡ መሆኑ ተሰምቷል። ብሪታንያ ፣ ፈረንሣይ፣ ጣሊያን ፣ ኔዘርላንድስ ፣ ግሪክ እና በርካታ የአውሮፓ ሀገራት በካርቱም የነበሩ ዜጐቻቸውን እያወጡ መሆኑን አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል ::


የአሜሪካ ልዩ የአየር ኃይል ባካሄደው ዘመቻ በመዲናዋ ካርቱም የነበሩ 70 የኤምባሲው ዲፕሎማቶችን እና ቤተሰቦቻቸውን ከከተማዋ በተሳካ ሁኔታ ማውጣት መቻሉን የአሜሪካ ባለስልጣናት አስታውቀዋል፡፡ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እንደ ኢትዮጵያ፣ ጅቡቲና ሳዑዲ አረቢያ ያሉ አገሮች ባይተባበሩን ኖሮ ዘመቻው ስኬታማ አይሆንም ነበር ብለዋል፡፡


ሳዑዲ አረቢያ በበኩልዋ በካርቱም የነበሩ 157 ዜጐቿን ባካሄደችው ዘመቻ በተሳካ ሁኔታ ማውጣት መቻሏን በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤትዋ በኩል አስታውቃለች ።
🇷🇺#ሩሲያ
የቡድን 7 ሀገራት በግንቦት ወር በጃፓን በሚያካሂዱት ጉባኤ ላይ ከአውሮፓ እና ከቡድን 7 ሀገራት ወደ ሩሲያ በሚላኩ የወጪ ምርቶች ላይ ሙሉ ክልከላ እንዲጣል በሚያስችለው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ሊመክሩ ማቀዳቸውን ሩሲያ ቱዴይ ዘግቧል፡፡በዚህም የቀድሞው የሩሲያ ፕሬዚዳንት ዲምትሪ ሜድቬዴቭ የበለፀጉት የቡድን 7 አገራት ወደ ሩሲያ የሚላኩ የወጪ ምርቶች ላይ እገዳ እንዳይጥሉና ማዕቀብ የሚጥሉ ከሆነ ሩሲያ ከዩክሬን ወደቦች እህል እንዲወጣ ከተደረሰው ዓለም አቀፍ ስምምነት ትወጣለች ሲሉ አስጠንቅቀዋል ።
🇸🇴#ሶማሊያ
የሶማሊያ መንግስት በአገሩ ተሰማርቶ ያለው የአፍሪካ ሕብረት የሰላም አስከባሪ ሃይል የቆይታ ጊዜ እንዲራዘም ፍላጐት እንዳለው ይፋ አድርጓል።
የሞቃዲሾ መንግስት የሰላም አስከባሪ ኃይል “አትሚስ” የቆይታ ጊዜ እንዲራዘምለት ጉዳዩ ለሚመለከታቸው የጐረቤት ሀገራት እና የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የማሳመን ሥራ እያካሄደ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የሶማሊያ ፈቃደኝነት የተሰማው የአፍሪካ ሕብረት የሰላም እና የፀጥታ ኮሚሽን በሶማሊያ ተሰማርቶ ያለውን የአፍሪካ ሕብረት የሰላም አስከባሪ ኃይል “አትሚስ” የቆይታ ጊዜ ላይ የፊታችን ረቡዕ ይመክራል ተብሎ በሚጠበቅበ
ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New