News

አዲስ ነገር – ጆ ባይደን በቀጣዩ 2024 በሚካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እንደሚወደሩ አስታወቁ ።

🇺🇸#አሜሪካ
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በቀጣዩ የአውሮፓውያኑ አመት 2024 በሚካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እንደሚወደሩ አስታወቁ ።
ፕሬዚዳንት ባይደን ከኤንቢሲ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ በአውሮፓውያኑ 2024 በሚካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እንደሚወዳደሩ ገልጸው ይሁንና በአጠቃላይ የፕሬዚዳንታዊ እጩነታቸው ዙሪያ ይፋዊ መግለጫ ለመስጠት እንዳልተዘጋጁ ነው የገለፁት፡፡
የዋይት ሀውስ ባለስልጣናት በፕሬዚዳንት ባይደን የቀጣይ የምርጫ ዘመቻ ዙሪያ የሚደረሰውን ውሳኔ ለሕዝብ ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ዘገባው የሮይተርስ ነው፡፡
🇦🇫#አፍጋኒስታን
የዓለም የምግብ ፕሮግራም በአፍጋኒስታን የሰብዓዊ ድጋፍ ለማቅረብ 800 ሚሊዮን ዶላር እንደሚፈልግ አስታወቀ ።
የዓለም የምግብ ፕሮግራም ከ25 አመታት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፍተኛ የሆነውን የ800 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ከለጋሽ አገራት ሲጠይቅ ድጋፉ ለሚቀጥሉት 6 ወራት በሀገሪቱ ላሉ ድጋፍ ፈላጊ ዜጐች የዕለት ደራሽ የምግብ እርዳታ ለማቅረብ የሚውል ነው ብሏል።
በአፍጋኒስታን የዘወትር ፈተና እየሆነ የመጣው የተፈጥሮ አደጋ እና ለአስርት አመታት የቀጠለው ጦርነት በተለይ በሀገሪቱ የሰብዓዊ ቀውሱ እንዲባባስ ማድረጉን ነው ተቋሙ ይፋ ያደረገው ። ዘገባው የአሶሺየትድ ፕሬስ ነው፡፡
🇬🇧#ብሪታንያ
ብሪታንያ፣ ዩክሬን ወድማ ከሀገርነት ወደ ምድረ በዳነት እንድትቀየር ፍላጐት አላት ስትል ሩሲያ ክስ አቀረበችባት፡፡
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ ብሪታንያ ዩክሬን ምድረ በዳ እንድትሆን ትፈልጋለች ያሉት የብሪታኒያ መንግስት ለኪየቭ የዩራኒየም ንጥረ ነገርን የያዘና በጦርነት ወቅት በተለይ ታንኮችን የማጋየት ኃይሉ ከፍተኛ እንደሆነ የሚነገርለትን የጦር መሳሪያ ወደ ዩክሬን ለመላክ ማቀዱን ተከትሎ ነው፡፡
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የብሪታንያ ውሳኔ ግጭት አባባሽ እና ብሪታንያ ዩክሬንን መልሶ ለመገንባት ከያዘችው እቅድ ጋር በቀጥታ የሚጋጭ ነው ብሏል፡፡
ዘገባው የአናዶሉ ነው፡፡

🇨🇳#ቻይና
የአፍሪካ ሀገራት የእዳ ሽግሽግ እንዲካሄድላቸው በሚደረገው ጥረት አሜሪካ ኃላፊነቷን እየተወጣች አይደለም ስትል ቻይና አስታወቀች፡፡
የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃለ አቀባይ ዋን ወንቢን ይሄን ያሉት የአሜሪካ እና የዓለም ባንክ ባለሥልጣናት አዳጊ ሀገራት የእዳ ሽግሽግ እንዲደረግላቸው በቀጠለው ጥረት ቻይና መሰናክል ሆናለች ማለታቸውን ተከትሎ ነው።
ቃለ አቀባዩ በቡድን 20 አገራት የጋራ ፍሬም ወርክ ማዕቀፍ አሰራር ስር አዳጊ አገራት የእዳ ሽግሽግ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማድረግ ረገድ ቻይና ጉልህ ሚና ተጫውታለች ነው ያሉት፡፡
ዋን ወንቢን በተለይ አሜሪካ አገራቱ የእዳ ስረዛም ሆነ የእዳ ሽግሽግ ተጠቃሚዎች እንዲሆኑ አበክራ ልትሰራ ይገባል ብለዋል፡፡
ዘገባው የአፍሪካ ኒውስ ነው።
🇸🇴#ሶማሊያ
የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ለሥራ ጉብኝት ሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ መግባታቸው ተሰማ፡፡
ዋና ፀሐፊው አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በሞቃዲሾ ጉብኝታቸው በሶማሊያ ለቀጠለው የከፋ የሰብዓዊ ቀውስ ምላሽ ለመስጠት በሚያስችሉ ድጋፎች ዙሪያ ከሀገሪቱ ባለስልጣናት ጋር ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል ::
የመንግስታቱ ድርጅት በሶማሊያ 8 ሚሊዮን ያክል ህዝብ የአስቸኳይ ድጋፍ ፈላጊ ነው ይላል በሪፖርቱ፡፡
ዘገባው የቢቢሲ ነው፡፡

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New